Agreement signed, Ethiopian will soon fly between Addis and Toronto Canada!
ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቶሮንቶ እንዲበር የሚያስችል የአየር አገልግሎት ስምምነት ተደረሰ

አዲስ አበባ, ጥር 14 ቀን 2002 (አዲስ አበባ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ካናዳ ቶሮንቶ እንዲበር የሚያስችል የአየር አገልግሎት ስምምነት ከካናዳ አየር አገልግሎት ጋር ተደረሰ፡፡
የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ እንዳመለከተው ስምምነቱ የተደረሰው ከጥር 4-6 ቀን 2002 ዓ/ም ካናዳ ውስጥ ነው፡፡
የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ እንዳመለከተው ስምምነቱ የተደረሰው ከጥር 4-6 ቀን 2002 ዓ/ም ካናዳ ውስጥ ነው፡፡
ስምምነቱ የተደረሰው በሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን ዳይሬክተር ጄኔራል በኮሌኔል ወሰንየለህ ሁነኛው በተመራ ቡድንና በካናዳ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የካናዳ አየር አገልግሎት ዋና ተደራዳሪ ሚስተር ሮበርት ረዱ መሆኑን መግለጫው አመልክቷል፡፡
ስምምነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሳምንት ሶስት ጊዜ ወደ ቶሮንቶ እንዲበር የሚያስችል ነው፡፡
በረራው በሁለቱ አገሮች መካከል የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና የቱሪዝም ግንኙነቶችን በማጠናከር ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው መግለጫው ጠቁሟል፡፡በካናዳ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አየር መንገዱ ወደ ካናዳ እንዲበር ለበርካታ ዓመታት ሲያቀርቡት ለነበረው ጥያቄ ስምምነቱ ምላሽ እንደሰጠም ገልጧል፡፡