በሐረር ቴሌቪዥን ተቃዋሚ"ዎችና ገዢው ፓርቲ እየተወነጃጀሉ ነው
በሐረር ቴሌቪዥን ተቃዋሚ"ዎችና ገዢው ፓርቲ እየተወነጃጀሉ ነው
(በአሰግድ ተፈራ) Reporter
በሐረሪ ክልል በምርጫ ተፎካካሪነት የቀረቡት የሐረር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ሐዲድ) እና የሐረር ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሐሕዴፓ) ጥምረት ፈጥረው የምርጫ ዘመቻ እያካሄዱ ባሉበት ወቅት የፓርቲያቸው አባላት ያልሆኑ ሰ"ዎች በክልሉ የቴሌቪዥን ስርጭት የስም ማጥፋት እንደፈጸሙባቸው አስታወቁ፡፡ የቴሌቪዥን ስርጭት ክፍሉ አስተባብሏል፡፡
የጥምረቱ አመራሮች ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደተናገሩት፣ የሐዲድ አባላት ያልሆኑ 14 ሰዎ"ች የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በመምሰል የፓርቲው አመራሮች ከኃላፊነት እንደወረዱ በማስመሰል በሐረር ክልል መገናኛ ብዙኃን ሥር በሚገኘው የኤፍ ኤም ሬዲዮ በ24/05/2002 ዓ.ም. እና በ28/05/2002 ዓ.ም.፣ በተጨማሪም በሐረሪ ቴሌቪዥን ክፍለ ጊዜ (በኢቲቪ) በአማርኛ የካቲት 1/02 ዓ.ም.፣ በኦሮምኛ የካቲት 3/02 ዓ.ም. እና በሐረሪኛ የካቲት 5 ቀን 2002 ዓ.ም. በተደጋጋሚ ለሦስት ቀናት አስተላልፈዋል፡፡
"የድርጅታችን ከፍተኛ አመራሮች በማስመሰል 14 ሰዎ"ችን በማስፈረም ከኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ዕውቅና የሌላቸውን በማሰባሰብ ሚዲያውም ያለ ምንም ማስረጃ መግለጫ እንዲሰጡ የተደረጉት ክፍሎች የድርጅታችን አባል ለመሆናቸው የሚገልጽ መታወቂያም ሆነ ማስረጃ የሌላቸው መሆኑን ጥምረቱ አብራርቷል፡፡ ድርጊቱም "በአንድ የፖለቲካ ፓርቲ ሕልውና መቀለድ ስለሆነ የምርጫ ቦርድ አጣርቶ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀናል" ብለዋል፡፡
በተጨማሪም የካቲት 18/02 ዓ.ም. በፖለቲካ ፓርቲ"ች የክርክር የአየር ሰዓት የክልሉ ገዢ ፓርቲ ሐብሊ "ተቃዋሚ"ችን ማለትም ሐዲድና ሐሕዴፓን ፀረ ዴሞክራሲ፣ ፀረ ሰላም እና ኪራይ ሰብሳቢ"ች፣ አገር ማስተዳደር ቀርቶ ራሳቸውንም ማስተዳደር ያልቻሉ ናቸው" በሚል የስም ማጥፋት ዘመቻ ማካሄዱንና የምርጫ የሥነ ምግባር መጣሱን ተናግረዋል፡፡
ቅሬታው የደረሰው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሐዲድ 15 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት እንዳሉት ገልጾ የፓርቲው ሊቀመንበር ስም፣ የውሳኔ ቃለ ጉባኤና የቀድሞው ሊቀመንበር ስም የማይመሳሰል በመሆኑ የፓርቲው አመራሮች ወርደዋል በሚል ተወስኖ የተላከለትን ቃለ ጉባኤ የፓርቲውን መተዳደሪያ ደንብ ያልተከተለ በመሆኑ ውሳኔውን ለመቀበል እንደሚቸገር ጠቅሶ ለእነ አቶ ሐሺም ሳሊህ ዓሊ በጻፈው ደብዳቤ አስታውቋል፡፡
የምርጫ ቦርድ ይህንን ቢልም በሐረር የቴሌቪዥን ስርጭት መግለጫ የሰጡት ክፍሎች የሐዲድ አመራሮች እንደሆኑና የስርጭት ጣቢያው ከፓርቲው ስለመወገዳቸው የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ሥራ አስኪያጁ አቶ መሐመድ ሻሳ ተናግረዋል፡፡ ፓርቲው ያቀረበውንም ቅሬታ አስተባብለዋል፡፡
"አንድ ዜና ወይም ሪፖርት ሲቀርብ መመጣጠንና ሚዛን መጠበቅ እንዳለበት እናምናለን" ያሉት ሥራ አስኪያጁ የፓርቲው አመራሮች እንዲወርዱ መደረጉን ገልጸው መግለጫ የሰጡት ክፍሎች የፓርቲው አባላት እንደሆኑ እንደሚያውቁ ተናግረዋል፡፡
የሐዲድ አመራሮችም ቢሆኑ መግለጫ የሰጡት ክፍሎች አባሎቻቸው እንደነበሩ አምነው ማስተባበያ መግለጫ በመስጠት የአየር ሽፋን እንደተሰጣቸው የተናገሩት አቶ መሐመድ፣ "ፓርቲው መብቴ ተነፍጓል ካለ መክሰስ ይችላል" ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ ዜና ሐዲድን በመወከል በጀጎል ልዩ የምርጫ ክልል ለክልል የሚወዳደሩት አቶ ኑረዲን አደም፣ "ለገዢው ፓርቲ የምርጫ ሥራ ከመንግሥት ሠራተኞች እንዲቆረጥ በተወሰነው መሠረት ያለፈቃዳቸው እንደተቆረጠባቸው ተናግረዋል፡፡
በሐረሪ ክልል በአዲሱ የአሠራር ማሻሻያ መሠረት ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ ደሞዙን ከንግድ ባንክ እንዲወሰድ ስለሚያዝ ደሞዛቸውን ሲቀበሉ አምስት ከመቶ እንደተቆረጠባቸው የገለ"ት አቶ ኑረዲን፣ "አሸንፈዋለሁ፡፡ በምርጫ ከሥልጣን አወርደዋለሁ ያልኩት ፓርቲ ከደሞዜ አምስት በመቶ በመቁረጥ የእኔን ፓርቲ ለማሸነፍ መወሰኑ አስገርሞኛል" ብለዋል፡፡
አቶ ኑረዲን የሚሠሩበት በሐረሪ ክልል የሥራና ከተማ ቢሮ ሥራ አሥኪያጅ የሆኑት አቶ ኤሊያስ አብዱል ማሊክ በበኩላቸው፣ "የመንግሥት ሥራና የፖለቲካ ሥራ የተለያየ በመሆኑ የፓርቲው አባላት በራሳቸው ውሳኔ ካደረጉት ውጪ ከማንኛውም ሠራተኛ ላይ አምስት በመቶ አልተቀነሰም" ካሉ በኋላ፣ አቶ ኑረዲንን ጨምሮ አራት የተቋሙ ሠራተኞች በቢፒአር የሥራ ሽግሽግ ምክንያት የሥራ መደባቸው ሲቀየር የመንቀሳቀሻ አበላቸው እንዲቋረጥ ተደርጓል" በማለት የአቶ ኑረዲንን መግለጫ አጣጥለዋል፡፡









